Tip:
Highlight text to annotate it
X
ድቮቲዎች ፈጣሪ እንዳለ ያውቃሉ:እርሱም “ብሃገቫን” ነው:
ፈጣሪ ብሃገቫን ይባላል:
ብሃገቨድ ጊታ የተነገረውም በክርሽና ነው:ሁሉም ሰው ያውቃል:
በብሃገቨድ ጊታም:በአንዳንድ ቦታ: "ብሃገቫን ኡቫቻ“ ተብሎ ተጠቅሷል:
ብሃገቫን እና ክርሽና አንድ ሰው ነው:”ክርሽናቱ ብሃገቫን ስቫያም“ (ሽብ 1 3 28)
ብሃገቫን:የዚህም የብሃገቫን ቃል ዝርዝር ተሰጥቷል:
”አይሽቫርያስያ ሳማግራስያ ቪራያስያ ያሻሳህ ሽሪያህግናና ቫይራግያዮሽ ቻይቫ ሳናም ብሃጋ ኢቲንጋና“ (ቪሽኑ ፑራና 6 5 47)
ብሃጋ:ከብሃግያቫን ቃልም ”ብሃግያን“ እንረዳለን:
ብሃግያ:ብሃግያቫን:ይህ ቃል ከብሃጋ የመጣ ነው:ብሃጋ ማለትም ሀብት ማለት ነው:
ሃብት ማለትም ብዙ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው ማለት ነው:አንድ ሰው እንዴት ነው ሀብታም ተብሎ ሊጠራው የሚችለው?
ገንዘብ ካለው:አእምሮ ካለው:ቁንጅና ካለው:
ዝና ካለው:እውቀት ካለው:ስግብግብነት ከሌለው:ይህ ነው ብሃገቫን የሚባለው:
እዚህም ብሃገቫን ስንል:ብሃገቫን ”ፓራም ኢሽቫራ“ ነው:
ሁለት ሁለት አይነት ቃላቶች አሉ:”ኢሽቫራ እና ፓራምኢሽቫራ“ ”አትማ እና ፓራምአትማ“ ”ብራህማን እና ፓራ ብራህማን“
የመጀመሪያው ተራ ሲሆን የሚቀጥለው ደግሞ አብይ ነው:
ለምሳሌ:ምግብ ስናዘጋጅ:የተለያየ ሩዝ ማዘጋጀት እንችላለን:
ሩዝ ይኖራል:የተለያዩ የሩዝ አይነቶችም ይኖራሉ:አና: ፓራማና:ፑሽፓና:ኪቾራና:እንደሚባሉት:
አብዩ አና:ፓራማና ይባላል:ፓራማ ማለት አብይ ወይንም ታላቅ ማለት ነው:
አና ሩዝ አለ:ነገር ግን አብይ ሆነ ማለት ነው:
የሩዝ ብትን: አብይ አይባልም:ሩዝ ብቻ ይሆናል:
ሩዝን ክሲራ ጋር ስታዘጋጁት ግን:ይህም ከወተት ጋር እና ከሌላ ጥሩ ነገሮች ጋር:ይህም “ፓራማና” ይባላል:
እንደዚሁም ሁሉ:የነፍስ እና የብሃገቫን ብህርዮች አንድ ናቸው:
ብሃገቫን ገላ አለው:እኛም ገላ አለን:
ብሃገቫን ነዋሪ ነው እኛም ነዋሪዎች ነን:
ብሃገቫን የመፍጠር ችሎታ አለው:እኛም የመፍጠር ችሎታ አለን:
ልዩነታችን ግን:እርሱ በጣም አብይ ነው:”ኤኮ ባሁናም ቪዳድሃቲ ካማን“
ብሃገቫን ይህንን ሁሉ ዩኒቨርስ ለመፍጠር ሲፈልግ:ከማንም እርዳታ አይፈልግም:
ሰማይን ይፈጥራል:ከሰማይም ቀጥሎ ድምጽን ይፈጥራል:
ከድምጽ ቀጥሎ አየር:ከአየር ቀጥሎ እሳት:
ከእሳት ቀጥሎ ውሃ:ከውሃ ቀጥሎ ደግሞ አፈር አለ: