Tip:
Highlight text to annotate it
X
ፍለጋ በአዲሱ Google ካርታዎች ውስጥ ከመቼውም በበለጠ ኃይለኛ ሆኗል።
እሱን ለመሞከር አንድ የተወሰነ ቦታ ይፈልጉና ከፍለጋ ሳጥኑ በታች ባሉት የመረጃ ካርዶች
ላይ የሚታየውን የአካባቢ መረጃን ይመልከቱ።
የሚፈልጉትን አውቀው ነገር ግን የት እንደሚያገኙት ግራ ገባዎት?
እንደ «ሴንትራል ፓርክ አጠገብ ያለ ቡና» ያሉ የቦታዎች ምድቦችን ፈልገው ይሞክሩ
እንዲያውም በጣም ተዛማጅ ውጤቶችን ለማግኘት ተዛማጅ ፍለጋዎችን ያያሉ።
ሁሉም የፍለጋ ውጤቶችዎ በዋናነት ከሚታየው የንግድ ስም ጋር በካርታው ላይ ይታያሉ።
ቀረብ ብለው ይመልከቱ፦ ልዩ አዶዎች የተለያዩ የንግዶች አይነቶችን እንዲለዩ ያግዙዎታል።
ትልልቆቹ ቀይ አዶዎች ለመጠይቅዎ በጣም ተገቢ የሆኑትን ውጤቶች ያመለክታሉ።
እያቀያየሩ በአዶዎች መካከል ጠቅ ሲያደርጉ ካርታዎ ከእያንዳንዱ አካባቢ ጋር የሚዛመዱትን መንገዶችን እና ቦታዎችን
ለማሳየት ሲስተካከል ያስተውሉ።
አንድ አካባቢ ሲመርጡ የመረጃ ካርዶች አጋዥ የሆኑ የንግድ መረጃዎችን ያሳያሉ።
ምርጥ ቦታውን ከመምረጥዎ በፊት የመንገድ እይታ ምስሎችን ይመልከቱ ወይም «ውስጥ ይመልከቱ»ን
ጠቅ በማድረግ ቀረብ ያለ እይታ ያግኙ።
የት እንደሚሄዱ ሲወስኑ አቅጣጫዎች፣ ሰዓቶች፣ ግምገማዎች እና ተጨማሪ ነገሮች የአንዲት ጠቅታ ርቀት ላይ ብቻ ናቸው።
አሁን በጣም ተገቢ የሆኑ መንገዶች እና ቦታዎች የሚታዩ በሚሆኑበት ጊዜ እዚያ እንዴት እንደሚደርሱ ግልጽ ነው።
ወደ ቤት እንዴት እንደሚኬድም እንዲሁ።
ከአዲሱ Google ካርታዎች ጋር ይተዋወቁ።