Tip:
Highlight text to annotate it
X
እንግዳ 1:የክርሽና ንቃት የመድረሻ አላማው ምንድን ነው?
ፕራብሁፓዳ:የመድረሻ አላማው
አይደለም:ለማለትም እምፈልገው:የመድረሻ አላማው:እንደምናውቀው በአለም ላይ: የመንፈስ እና የአለማዊ ንጥረ ነገሮች አሉ:
ምድራዊ አለም እንደአለም ሁሉ መንፈሳዊ አለምም አለ:
”ፓራስ ታስማት ቱ ብሃቫህ አንያህ አቭያክታህ አቭያክታት ሳናታናሃ (ብጊ8 20)
መንፈሳዊ አለም: ዘለአለማዊ ነው:ይህ ምድራዊ አለም ደግሞ: ግዜያዊ ነው:
እኛ ደግሞ መንፈሳዊ ነፍስ ነን:ዘለአለማዊም ነን:
ስለዚህ የእኛ ጥረት ሁሉ ወደ መንፈሳዊ አለም ለመመለስ ነው:
በዚህ አለም ላይ ቀርተን:ገላችንን ከመጥፎ መጥፎ ወይንም ወደ ጥሩ አለማዊ ገላ እየለዋወጡ ለመኖር: ምንም ምኞት የለንም:
ይህ ነው የእኛ ስራ:ይህ አለም ህመማችን ነው:
የእኛ ጤነኛ ህይወት የዘላለማዊ ኑሮን ስንደሰት ነው:
“ያድ ጋትቫ ና ኒቫርታንቴ ታድ ድሃማ ፓራማም ማማ” (ብጊ15 6)
አያችሁ?ይህ የሰው ህይወታችንንም:ይህን ብቁ የሆነ ደረጃን ለማግኘትን: ጥረት ለማድረግ እንድንጠቀምበት ያስፈልጋል:
ለሚለዋወጥ ነገር: ሌላ አለማዊ ገላ ይዘን እንድንወለድም ጥረት ማድረግ አይገባንም:ይህ ነው የህይወታችን አላማ:
እንግዳ 3:ይህ ለመንፈሳዊነት ብቁ መሆን: በአንድ የሰው እድሜ ይቻላልን?
ፕራብሁፓዳ:አዎን እንዲያውም በአንድ አፍታ ወይንም ቅፅበት ይቻላል:ይህም ከተስማማችሁ ነው:
ክርሽና እንዲህ ብሏል:“ሳርቫ ድሃርማን ፓሪትያጅያ ማም ኤካም ሻራናም ቭራጃ አሃም ትቫም ሳርቫ ፓፔብህዮ ሞክሺያዪሽያሚ ማ ሹቻሃ” (ብጊ18 66)
በዚህ አለም ገላችንን የምንቀያይረው:በሀጥያታዊ ተግባራችን ነው:
ነገር ግን ለክርሽና ሙሉ ልቦናችንን ከሰጠን እና የክርሽና ንቃትን ከወሰድን:በአንድ አፍታ ወይንም በቅፅበት ወድ መንፈሳዊ መድረክ መስፈር እንችላለን:
“ማም ቻዮ ቭያብሂቻሬና ብሃክቲ ዮጌና ሴቫቴ ሳጉናን ሳማቲያይታን ብራህማ ብሁያያ ካልፓቴ” (ብጊ14 26)
ልክ ንጹህ የሆነ ድቮቲ ደረጃ ላይ እንደደረሳችሁ:ይህን የአለማዊ ጉጉቶችን በቀላሉ ለማለፍ ትችላላችሁ:
“ብራህማ ብሁያያ ካልፓቴ” በመንፈሳዊ መድረክም ላይ ትሰፍራላችሁ:
በዚህም በመንፈሳዊ መድረክ ላይ ህይወታችሁን ብታልፉ:በቀጥታ ወደ መንፈሳዊ አለም ትሄዳላችሁ: